top of page

            የሌዋወያን መንግስት ማእከል እሴትቻችን እና ግቦቻችን

 

እሴቶቻችን (Our core values)

 የአሁኑን የእግዚአብሄር እውነቶች ( Present-Truth) በሃዋሪያዊው ተልእኮና ማህበረሰብ አማካኝነት የኢየሱስ ስም ፣ ማንነት ፣ባህሪውን እና ቃሉን ከፍ ለማድረግና አሁን ባለችው ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን የተሃድሶ ተግባር በማከናወን አዲስ መለኮታዊ ድፍረትና ብቃትን የተላበስችና የእግዚአብሄርን ፈቃድ እና ሃሳብ እስከፍጻሜ ማድረስ የምትችል ቤተክርስቲያንን ማዘጋጀትና መገንባት ነው።

 እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አባል በእግዚአብሄር ቃል በተገለጸው መሰረት የእግዚአብሄር መንግስት የሚጠይቀውን የህይወት አካሄድ (Life stayle) መተግበር ይጠበቅበታል ። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከማወቅ እና ከመረዳት እንዲሁም በቃል ከመናገር ያለፈን በትክክል በህይወት በመጓዝና በመኖር የሚገልጥ ስብእና ይጠበቅበታል።  ሁሉም ኣባል አሁን ካለበት የግል የይወት አቋም (ባህሪው ፣አስተሳሰቡ እይታው ---ወዘተ) ላቅ ወዳለ የእግዚአብሄር መንግስት እሴቶች (kingdom Values) ለመሸጋገር የሚጠይቀውን የለውጥ ሂደት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል ።ይህንንም የመለውጥ ሂደት (Transformation process) ተግባራዊ የሚያደርግበት ዋናው መንገድ ለራስ ፍላጎት ፣ለግላዊ ሀሳብ እና መሻት በመሞት የህወት ሂደት ነው። Process of death to self desire and personal ambition)

        አምልኮ ጸሎት እና የኣግዚአብሄርን ቃል ማንበብና ማጥናት ዋና የህይወት ማንነታችን ናቸው።

 የአምልኮ  ጅማሬ ቃሉ በህይወታችን ሲገለጥ ነው!  አምልኮ በተሰጠ ህይወት ማንነት (unreserved and fully commited life style) በመካከላችን ከፍ ያለ የእግዚአብሄር መገኝትን የሚጋብዝና አከባቢያችንንም በመንፈሳዊ ስርዓት ውስጥ እንዲሆን የሚቃኝ ነው ። በግልም ሆነ በጋራ የምናደርገው ጸሎት ውስጣዊው ባህሪው መገዛት የተሞላ ሲሆን ይህም ጸሎት የእግዚኣቢሄርን ፍቃድ እና ሀሳብ ባለመከልከል በሀይልና በብርታት በምድር ሁሉ እንዲተገበር የሚያደርግ ነው።  የእግዚኣቢሄር ቃል በሁሉም ሁኔታ ውስጥ የበላይነት ያለው የማይለወጥ የሚሰራ የህይወት መርህና የእምነት መሰረታችን እንደሆነ እናምናለን

        እንቅስቃሴ ከሌለው ስለራስ እቅዶች እና አሰራሮች ከተያዘ ሀይማኖታዊ ስርዓት በመውጣትና በመራቅ የእግዚአብሄርን የዘላለም እቅዶች እና ሀሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ ወደሚያስችለን ጉዞ በመፍሰስ ከፍ ወዳለው ወደ በወቅቱ እግዚአብሄር እንድንደርስበት ወደሚፈልገው የህይወትና የአሰራር አቋም የመከተልና የመተገበር አመለካከት እና አስተሳሰብ መገንባት ከሁሉም አባል የሚጠበቅ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን ዝቅ ኣድርጎ የእግዚአብሄር ሀሳብና ፍቃድ እንዳገለገለ ሁሉም አባል ይህንን የክርስቶስን ምሳሌነት ተግባራዊ በማድረግ የእግዚአብሄር ሀሳብና ፍቃድ በሙሉ ልብና ፍቃደኝነት ማገልገል ይጠበቅበታል።

      እግዚአብሄር አብ ፣ወልድ ፣መንፈስ ቁዱስ በሶስትነት የሚገለት አምላክ ሲሆን እኛም በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠራችን እርሰ በእርሳችን በመተባበርና በመደጋገፍ ትኽኽለኛ የሆነ ማህበረሰብ (community) መገንባት ይጠበቅብናል።ትክክለኛ እድገት የሚከሰተው እያንዳንዱ አባል የሚጠበቅበትን ማንኛውንም ነገር በትጋት በፍቅር ሌላው አባል እና ለሁሉም አካል አስተዋጽኦ ሲያደርግ ነው ስለዚህ ሂወትን ማካፈል ከሁሉም አባል የሚጠበቅ አንዱና ዋና ኣስፈላጊ የህይወት አካሄድ ነው።

     የሌዋውያን መንግስት ማእከል ከስዊዘርላንድ እና ከዛም ባለፈ ተልኮ በሀዋሪያዊ መርህ የተሀድሶን ስራ በቤተክርስትያን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ከእግዚአብሄር የተቀበለው ስራ በመሆኑ እያንዳኣንዱ አባል ይህንን ሊተገብር የሚችል ማንነት እንዲገነባ ይጠበቅበታል ።ይህም ማንነት ፉጹም በተሰጠ የህይወት አካሄድ በእግዚአብሄር የዘመን ፍጻሜ አገዛዝ የተሀድሶን እውነት የሚያውጅ እና ውስንነት ካለው ጠባብ አመለካከት በመውጣት አለም አቀፍ በሆነው የእግዚአብሄርን አመለካከት ለእግዚኣቢሄር መንግስት -ጸር የሆነውን የዚህን አለም አሰራርና መዋቅር ለማፈራረስ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ።

  ዋና ዋና ግቦቻችን (Our primary Objectieves)

 በእግዚአብሄር ፍቃድ እና ሀሳብ በጠንካራ መሰረት የሚገነባና የሚተገብር መጽሀፍ ቁዱሳዊ አመራርና እውን የሚያደርግ የእግዚኣቢሄር መንግስት ማህበረሰብ (kingdom community )ማዘጋጀት እና መስራት። የቤተክርስትያን መሰረት የሆኑትን የሀወሪያት እና የነቢያት አገልግሎት ስጦታዎችሁን በመቀበል እንዲሰሩ በመፍቀድ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች (ወንጌላዊ ፣መጋቢ አስተማሪ )አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ ብስለት እና ጥንካሬን (maturity and strength ) የተላበሰ ማህበረሰብ መገንባት። የኢየሱስ ክርስቶስን ባህሪ እና ማንነትን በመውረስ የትንቢት ፣መለኮታዊ ፈውስ ተአምራቶች እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የሚሰሩበትንና እያንዳንዱ ቤተሰብ እና አባል ፣በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሀይል እውነተኛ የህይወት ለውጥና ማንነት እንዲኖረው መትጋት። የሌዋውያን መንግስት ማእከል እውነተኛ እና ትክክል የህይወትና የአሰራር አካሄድ በመገንባትና በማነጽ ለሌሎች ማህበረሰብ (kingdom community) አርአያ ሊሆን የሚያስችልን ማንነትና አሰራርንመገንባት ናችው።

bottom of page