

ABOUT US
የሌዋውያን መንግስት ማዕከል
OUR VISION
I'm a paragraph. Click here to add your own text and edit me. I’m a great place for you to tell a story and let your users know a little more about you.
WHAT WE DO
I'm a paragraph. Click here to add your own text and edit me. I’m a great place for you to tell a story and let your users know a little more about you.
OUR COMMUNITY
I'm a paragraph. Click here to add your own text and edit me. I’m a great place for you to tell a story and let your users know a little more about you.
የሌዋውያን መንግስት ማእከል በዋና መሪው ( senior elder ) በበረከት ረታ እና በረዳት መሪው (asociate elder) መብራህቱ ገብረእግዚአብሄር የሚመራ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1999 ጀምሮ በስንጋለን ከተማ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ሲሆን በኮንግረስ WBN አለም አቀፍ መረብ አሰራር ውስጥ ፕሬዝደንት በሆኑት በዶክተር ኖኤል ውድሩፍ ሀዋርያዊ ጸጋ ጥላ ስር የሚመራ የአለም አቀፉ መረብ አስራር አካል እና ኮር ማህበረሰብ ነው።
ማህበረሰቡ በተለይ አሁን ባለንበት ወቅት የክርስቶስ አካል ለዘመን ፍጻሜ በምታደርገው የመጨረሻ ጉዞ መንገድ ጠራጊ የሆነውን ሐዋርያዊ ጸጋ በማወጅ እና ትንቢታዊውን የእግዚአብሄርን የዘለአለም ሀሳብ ለመፈጸም የሚያስችል ሐዋርያዊ ትውልድን በማፍራት ላይ ያለ ማህበረሰብ ሲሆን ለግዜው በምስራቅ ስዊዘርላንድ የሚገኝ ኢትየጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ያካተተ አለም አቀፍ አመለካከት ያለው ማህበረሰብ (ቤተክርስቲያን) ነው።
የሌዋውያን መንግስት ማእከል በውስጡ ልዩ ልዩ ቅርጽን የያዘ ደረጃውን በጠበቀ አመራር የታጀበ ሲሆን በወንዶች ፥በሴቶች ፥በወጣቶች ፥ በህጻናት ፥በትምህርት ፥ በግንኙነት ስርጭት፥በጸሎት፥በፕሮቶኮል፥በአስተዳደር በዝማሬ፥ በስፖርት እና በተለያዩ አገልግሎቶች ለማህበረሰቡ እና ለሌሎች አገልግሎትን ይሰጣል ። ወደ ዘመን ፍጻሜ እየተጠጋን ስንሄድ በእግዚአብሄር የዘለአለም ሀሳብ ውስጥ የተሰወረውን እና አሁን እግዚአብሄር ቤተክርስቲያንን በሰማያዊ ስፍራ ላሉት ለአለቆች እና ስልጣናት ትታወቅ ዘንድ ጥብቡን ለቤተክርስቲያን እየለቀቀ ባለበት በዚህ ሀዋርያዊ ጸጋ የህይወት ግንባታን ቀዳሚነት የሚሰጠው መሆኑን በመረዳት የሌዋውያን መንግስት ማእከል ትክክለኛ የሆኑ የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎችን (ወንዶችን ፥ሴቶችን ፥ቤተሰብን፥ ወጣቶችን እና ህጻናትን) ለማፍራት በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የተቀበሩትን እውነቶችን ፈልጎ በማግኘት እንዲሁም የእግዚአብሄር መንግስት ዜጎች ወደተጠሩበት የህይወት ልክ ለማምጣት ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል። እንዲሁም የጨለማው አሰራር እየጨመረ ባለበት እና በክርስቶስን አካል ላይ እንኳን ሳይቀር በጉስቅልና የተገለጥውን የፊት መጨማደድ ለማስወገድ የሀዋሪያዊው ተሀድሶ መልእክት በማወጅ እና በማስተማር ቤተክርስቲያን ቀድሞ ወደታሰበላት እና የጥንት የእምነት አባቶቻችን ወደ ተራመዱበት እውነት ለመመለስ የሚያስችለንን በየወቅቱ ከእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የሚገለጡትን የእግዚአብሄር መንግስት እሴቶች በመኖር እና በማወጅ ቤተክርስቲያንን በቀጣይነት ውበት ለማላበስ እና ለፍጻሜ ለማዘጋጀት ተግቶ መስራት ሌላው አንዱ ዋናው የሌዋውያን መንግስት ማእከል የእንቅስቃሴ መገለጫ ባህሪ ነው ።
ትኩረት የምንሰጣቸው እውነታዎች።
የእግዚአብሄር ቃል ሳይሸራረፍ እና ሳይበረዝ በንጽህና ለማህበረስቡም ሆነ ለአካሉ መልቀቅ ። በሙሉ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄር እራሱን የገለጠበት
( አብ ፥በወልድ ፥መንፈስ ቅዱስ) ማነንት (ባህሪ) እና እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ በኩል ለቤተክርስቲያን የተሰጡትን ስጦታዎች ሙሉ በሙሉ በመቀበል መኖር፥ማድረግ እና ማስተማር ። የእግዚአብሄር ቃል በሚያዘው የቅድስና ህይወት ልክ መኖር እና በእግዚአብሄር ፊት ያለነቀፋ ለመሆን አጥብቆ መስራት። ሐዋርያዊ ትውልድ እንደመሆናችን መጠን ከግለኝነት ይልቅ ለጋራ ትስስር ህብረት እና ድርጊት ትልቅ ትኩረት መስጠት። እያንዳንዱ አባል በክርስቶስ ጸጋ እና ሀይል እውነተኛ ህይወት ለውጥ እና ማንነት ኖሮት መለኮታዊውን ሀሳብ በመረዳት ብስለትን የተሞላን ህይወት ከመላበስ በመነሳት የጌታን ሀሳብ በትክክል መተግበር ወደሚችሉበት የህይወት ልክ ማምጣት። በማህበረሰቡም ሆነ በአለም አቀፍ እንቅስቃሴያችን በእግዚአብሄር ፊት በተቀመጠው መርሆ መሰረት በአመራር ውስጥ ያለውን ድንበር በቀጣይነት በመጠበቅ መኖር።